Abu Humeyra
እናቴ አወሊያ
የእናት መከራ ማለቂያ የለው እንዲሉ ብዙ ልጆችን የወለደችና የምትወድደው ባሏ የሞተባት አንዲት እናት ነበረች፡፡ይህች እናት ልጆችን እንደ እናትም እንዳበትም ሆና ለማሳደግ ቀን በፀሀይ ሌሊት በቁር ላይ ታች ትባዝን ነበር፡፡ግና የገንዘብ እንጂ የፍቅር ደሀ አልነበረችምና የማያልቀው የናትነት ፍቅሯ ለጨለማው ቤታቸው ብርሀን ነበር፡፡ሲገኝ በልተው ሲጠፋም ተጫውተው ህይወትን ያጣጥሟት ነበር፡፡ቤታቸው የፍቅር ፡የደስታ ና የመከባበር ባንዲራ ሁሌም እንደተውለበለበ ነበር፡፡ ሰው ሁሉ ስለዛ ቤት ፍቅር ያወራ ጀመር፡፡ታዲያ ለሷ አሳቢ ነን ያሉ ቤተ ዘመዶቿ ምንም ሳይራሩ ያለ ፍላጎቷ ለአንድ ክፉ ባል ዳሯት፡፡ ይህ ባል ግዴለሽ፣ ገንዘብ ወዳድ፣ ጠጥቶ ከመስከር፣ በልቶ ከመጥገብ፣ በስተቀር ሌላ ሞያ የሌለው ነው፡፡ ሲወጣ ሲገባ ይደበድባታል፡፡ እንጨት ሽጣ፣ ኩበት ለቅማ፣ እንጀራ ጋግራ፣ ያጠራቀመቻትን ገንዘብ ነጥቆ ይወስድባታል፡፡ እንደፈለገም ይረጨዋል፡፡ ታዲያ ይህች እናት በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ በመከራዋ ላይ መከራ ተደራረበባት፡፡ታዲያ ከዚህ መከራ ሸሸት የት ትሂድ? የአካባቢው ሕግ፣ ባህሉ እና ልማዱ፣ በሙሉ የእርሷን ሮሮ እና ልመና የሚሰማ እንጂ የሚረዳ ፡የሚያይ እንጂ የሚመለከት አልሆነም፡፡ ዘመዴ ያለቻቸውም እዚህ እሳት ውስጥ ከተዋት ጀርባቸውን ሠጥጠዋታል፡፡ሁሉም እርሱን እንደ ሕጋዊ ባልዋ ነውና የሚቆጥሩት ከርሷ ይልቅ እሱ ነው የሚሰሙት፡፡ ታዲያ የት ሂዳ መከራዋን ትናገር ? የትስ ሂዳ ከችግሩ ትገላገል?
ይህ ክፉ ባልዋ እርሷን ብቻ ሳይሆን ልጆቿንም ያሰቃያቸው ጀመር፡፡ እነርሱም በዚያ ቤት ውስጥ መከራውን እና ስቃዩን፣ ረሃቡን እና ጭቅጭቁን እየሰሙ መኖር መረራቸው፡፡ የእንጀራ አባትየው የስካር በትር በማይችል ትከሻቸው ላይ ያርፍ ጀመር፡፡ በቤቱ ይውለበለብ የነበረው የሰላም የፍቅር ባንዲራ ወረደ፡፡ ምንጊዜም የሚሰማው ክፉ እና ልብ የሚያደማ ነገር ሆነ፡፡ ሰው ሁሉ ስለዚያ ቤት ረብሻ ያወራል፡፡ ልጆቹ በዚህ ክፉኛ ተጎዱ ፡፡በመንገድ ላይ ሰው ሲያገኛቸው ስለ ቤታቸው ይጠይቃቸዋል፡፡ እነርሱም በሃፍረት ይሸማቀቃሉ፡፡ ስለዚህም እናታቸውን ጥለው ወደ ሌላ ቦታ መሄድና ስለዚያ ቤት ከማያስቡበት እና ከማይሰሙበት ቦታ ለመሄድ ፈለጉ፡፡ የሚችሉትን ያህል እየሠሩ፣ ለራሳቸው የሚበቃቸውን እየኖሩ፣ መከራውን መገላገል እና እፎይ ብለው መኖር አሰኛቸው፡፡